እኛ የምንሰራው

አንዳንዴ ከባድ ሁኔታ ፣ችግር ወይንም ግራ በመጋባት አይነት ስሜት ውስጥ እንሆናለን ፡ የሆነ ቦታ ላይ የቆምን አይነት ሰሜትም ይሰማናል። ህይወታችን እንዴት ወደ ፊት መሄድ እንዳለበት እና ምን ማድረግ እንዳለብንም አናውቅም።
አንዳንዴ ያለንበትን ሁኔታ ለማሻሻል ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ይገባናል
አንዳንዴ የምናወራው ሰው እንፈልጋለን

የምናምነው፣ ሚስጥራችንን የሚጠብቅልን እና በአግባቡ ቦታ ሰጥቶ የሚሰማን ሰው እንፈልጋለን
የህይወታችንን ከባዱን ክፍል የምናጋራው ወይንም የምንነግረው ሰው እንፈልጋለን
ባለሞያ የሆነ እና ልምዱ ያለው ሰው

አሰቃቂ የሆነ የህይወት ተሞክሮ፣ግላዊ የሆኑ ችግሮች፣ የቤተሰብ ግጭት፣የአይምሮ ውጥረት፣ የእንቅልፍ የማጣት ችግር እና አስቸጋሪ የሆኑ የህይወት ሽግግሮች\ለውጦች ያሉ ከሌሎች ሰዎች እንድንርቅ ወይንም እንድንገለል ሊያደርጉን ይችላሉ።

ነገሮችን ከግንዛቤ ውስጥ ከቶ እራስን በመገምገም ሂደት ውስጥ የሚደረግ የራስ እድሳት እና ንግግሮች ድፍረት እና ሃይል ይሰጠናል እንዲሁም ለችግሮቻችን መፍትሄ ወደማግኛ የሚወስደንን መንገድ እንድናገኝ እናም ከሃብቶቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት እንደገና እንድናድስ ይረዳናል።

በሚገባ የሰለጠኑ የipso-care ባለሞያዎቻችን/አማካሪዎቻችን እርሶን ለማገዝ እዚህ ይገኛሉ።

አሁኑኑ ይመዝገቡ እና አገልግሎቱን ያግኙ

Ipso care

ወደ ድህረ-ገፃችን በመግባት ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ፣ ፍፁም ርህራሄ የተላበሱ እና እንዲሁም እራሳቸውን ለስራችው የሰጡ አማካሪዎቻችንን ያግኙ። አማካሪዎቻችን ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ሲሆኑ እርሶን ለማገዝ እዚህ ይገኛሉ፡ በአስቸጋሪ የህይወት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም እንኳን ወደ ግላዊ እና ማህበራዊ ደህንነት የሚወስደወን መንገዶትን እንዲያገኙ እርሶን ለመርዳት እዚህ ይጠብቆዎታል።

አላማችን ሰዎች ችግሮቻቸውን እና ግጭቶቻቸውን መፍታት እንዲችሉ ማስቻል እና ከቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ እንዲሁም ከሚወድዋቸው ጋር ተግባራዊ እና የሚክስ/አስደሳች ግንኙነት መፍጠር/ማጎልበት እንዲችሉ ማገዘ ነው። በተጨማሪም ሰዎች በራሳቸው እሴቶች ላይ በተመሰረተ መልኩ በህይወታቸው ላይ ተፅእኖ እንዲፈጥሩ እናም ለማድረግ እንዲወስኑ ማገዝ ነው።

የእኛ የምክር አገልግሎት ሀብቶቻችን እና ችግሮችን መፍታት ላይ ያተኮረ ሲሆን እንዲሁም ድጋፍ የሚሰጥ፣ ከፍርድ ነፃ የሆነ እና ሚስጥራዊነትንም የጠበቀ ነው

የ ipso-care አማካሪዎቻችን በሚገባ የሰለጠኑ ባለሞያዎች ሲሆኑ በተጨማሪም በአይምሮ ጤና ዘርፍ የላቀ እውቀት ባላቸው ባለሞያዎች በማያቋርጥ መልኩ ክትትል ይደረግላቸዋል

Ipso-care ሚስጥራዊነትን የጠበቀ፣ግላዊ እና ደንበኛ ተኮር የሆነ Tele-video ክፍለ ግዜ አገልግሎት ይሰጣል

ራዕይ እና ተልእኮ

ራዕያችን

እምነት የሚጣልበት ፣ አስተማማኝ የሆነ፣ሞያዊ እንክብካቤ የተሞላበት፣ምቹ የሆነ፣ በየትኛውም የእድሜ ክልል ወይንም የኑሮ ደረጃ ላለ፣ እንዲሁም ከየትኛውም አይነት ጎሳ ወይም መንፈሳዊ ወጎች ለመጣ የመስመር ላይ የመክር አገልግሎት መፍጠር ነው።

ተልእኮ

ምኞታችን ለአለም የበኩላችንን ድጋፍ ማበርከት ሲሆን፣ ይህም ሰዎች ንቁ፣ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው፣ ስለራሳቸው እና ስለአካባቢያቸው ሃላፊነቱን የሚወስዱ እንዲሆኑ እና እንዲሁም ስለሌሎች እና ስለአለአም በፍቅር፣ ማወቅ በመፈለግ ጉጉት፣የሌላውን ችግር ለመረዳት ዝግጁነት ባለው መልኩ መወያየት እንዲችሉ ድጋፍ ማድረግ ነው። እራሳቸውን ለሞያቸው ከሰጡ ከባለሞያዎቻችን እና ቡድናቸን ጋር በመሆን ባህላዊ የሆኑ አገላለፆች(የእራሳችንን አስተሳሰብ እና ስሜት የምናስተዋውቅበት ሂደት) እና ነፀብራቆችን(ነገሮችን ከግምት ውስጥ በመክተት እራስን መገምገም) እናበረታታለን። እርሶን ለማገዝ እዚህ እንገኛለን።

መመሪያዎች

ግለሰባዊ እና አካባቢያዊ የባህል አገላለፆች፣ ባህሎችን፣ ውይይቶችን እና የግል እንዲሁም የጋራ እሴቶችን ነፀብራቆችን እናበረታታለን

መርህሆቻችን የምንላቸው የሚከተሉት ሲሆኑ፥ እኚህም ተጠያቂንት፣ ግልፅነት፣ሃሳብን የመግለፆ ነፃነት፣ እኩል መብቶች፣ ሰላም እና በግለስብ እንዲሁም በጋራ የሆኑ እርቆች ናቸው።